Welcome to FMHACA

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ስለጤና ቁጥጥር ለባለድርሻ አካላት እና ለኢንተለጀንሲ እና ሰርቪላንስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡ New

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በአዳማ ከተማ ለባለድርሻ አካላት እና ለመስሪያቤቱ የሰርቪላንስ እና የኢንተለጀንሲ ባለሙያዎች ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 4/2010 ዓ.ም. በሕገወጥ የጤና ግብአት እና አገልግሎት ቁጥጥር እና በቅንጅታዊ አሠራር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የባለስልጣን መስሪያቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ እንደገለጹት የሕገወጥ የምግብ የመድኃኒት እና የጤና አገልግሎት ንግድና ዝውውርን ለመቆጣጠር የባለድርሻ አካላት እና የባለስልጣኑን የኢንተለጀንስ እና ሰርቪላንስ አቅም በመገንባት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሠራርን በማጎልበት በመናበብ መሥስራት እንደሚያስችል በመግለጽ፤ በመግቢያና መውጫ ኬላዎች አካባቢ የሚታዩ አንዳንድ አለመናበቦችን ለማስቀረት እና ቅንጅታዊ አሠራሮችን ለማጠናከር ስልጠናው እንደተዘጋጀ አስታውቀዋል፡፡

 

በማያያዝም የኢንተለጀንሲ እና ሰርቪላንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አኖሴ እንዳሉት ስልጠናው ከሥራቸው ጋር ተያያዥነት ያለው ሆኖ በጥራት ምርመራ ሲስተም፣ በሥራ ምዘና (BSC)፣ በምግብ ምዝገባ፣ በመድኃኒት ምዝገባ፣ ተመሳስለውና ከደረጃቸው በታች በተመረቱ መድኃኒቶች እና በኢንተለጀንሲ ዙሪያ መሆኑ ታውቋል፡፡ የስልጠናው አላማ ወቅቱ ከሚጠይቀው ቴክኖሎጂና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ለመራመድ ሠራተኞችን በየግዜው በማብቃት የአቅም ክፍተት መሙላትና ክህሎትን ማዳበር ነው፡፡

ተሳታፊዎች እንዳስታወቁት ሥልጠናው ለሚሰሩት ሥራ አጋዥነቱ የጎላ መሆኑንና  የልምድ ልውውጥ በማድረጋቸው ዕውቀት እንዳገኙበት በመግለጽ፤ በየግዜው ይህ ዓይነቱ ገንቢ ሥልጠና ለተቆጣጣሪ አካላት ቢሰጥ ሃገሪቷ የሰለጠነ ተቆጣጣሪ ኃይል ይኖራታል ሲሉ ሐሳባቸዉን አካፍለዉናል፡፡ በአጠቃላይ ስልጠናው ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው እና በቀጣይ ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ጋር በመሆን በህብረተሰቡ ላይ የጤና መጓደል ሊያስከትሉ የሚችሉ ግብአቶች እና አገልግሎቶችን ለመቆጣጠርና በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በቅንጅት ለመስራት መነሳታቸው እና ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

 

Comments / Feedback  •   • 

Note: To view, save/download, or print the following files, you must have Adobe Acrobat Reader installed on your computer.
Click here to download Adobe Acrobat Reader.