Welcome to FMHACA

በባለስልጣን መስሪያቤቱ እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ቢሮ የንግድና ሸማቾች ጥበቃ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ስልጠና ተሰጠ፡፡ New

 

የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና  ቁጥጥር ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ቢሮ የንግድና ሸማቾች ጥበቃ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበበር ለሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎችና ኢንስፔክተሮች በተቋማቱ ህጎች እና አሰራሮች እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር በአዳም ከተማ ለአራት ተከታተይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ለሰልጣኞቹ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የባለሰልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ የሁሉ ደነቀው በሀገሪቱ እየታየ ካለው እድገት ጋር ተያይዞ በምግብ በመድሃኒትና በጤና አገልግሎት ዘርፍ በማምረት፣ በማስመጣት እንዲሁም በመላክ ላይ የሚሰማሩ ዜጎች እየበዙ መጥተዋል ብለዋል፡፡ በዛው ልክ ቁጥጥሩ እየተወሳሰበ እና በህገወጥ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መከላከልና መጠበቅ እንደሚገባ፤ እንዲሁም በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱትን አምራቾች፣ አስመጪዎችንና ላኪዎች ጋር በመተባበር ህገወጦችን በተለይም ለራሳቸው ጥቅም እንጂ ለህዝብ ጤና ምንም ደንታ የሌላቸው ህገወጦችን  በመከታተልና በመቆጣጠር ለህግ በማቅረብ እንዲታረሙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ህገወጦች አካሄዳቸውን እና ስልታቸውን ስለሚቀያይሩ በዚያው ልክ ተቀናጅቶ እና ተደራጅቶ ለመስራት በሁለቱም ተቋማት የሚገኙ ባለሙያዎች ክህሎት እንዲሁም በህጎቹ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የተጠናከረ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የስልጠናው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ  አስታውቀዋል፡፡

 

የመክፈቻ ንግግር  ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ነጋ አደሬ አንደገለጹት የጋራ ችግሮችን በመለየት ሁለቱንም ተቋማት ለማሸጋገር የየራሳቸውን የአሰራር እና የህግ የክሎትና የአቅም ውስንነት በመለየት አንዱ የሌላውን በመደገፍ  ለባለስልጣኑ የቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ መርማሪዎችን  በማብቃት የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥለውን የህገወጥ የምግብ የመድኃኒትና የጤና አገልግሎት ንግድና ዝውውርን በብቃት ለመቆጣጠር፣ ለመከላከል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም አጥፊዎችን ለህግ የማቅረብ ስራውን ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሁለቱ ተቋማት ቁጥጥር እና ምርምራ የሚደረግባቸው ወንጀሎች በስፋት ህብረተሰቡ የሚጠበቅባቸው ምርቶች እነዚህም ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጣሸቀጦች ላይ የሚከሰት መሆኑ በዘርፉ የሚከሰቱ ወንጀሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ላለው ሽብርተኝነት የገቢ ምንጭ ሆነው በማገልገል ላይ በመሆናቸው የእነዚህን ሀገራዊ እና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች መረብ በመበጣጠስ የሀገርን ደህነንነት እና የቀጠናውንና የአለም አቀፍ  ሰላም  ግንባታ በተቋማቱ በቅንጅት ተባብሮና ተደጋግፎ የሚሰራው ቁጥጥር እና መከላከል ሰላምን ማስጠበቅ ይቻላል ብለዋል፡፡
ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ቢሮ የንግድ እና ሸማቾች ጥበቃ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለመጡ መርማሪዎች እና የባለስልጣኑ የቁጥጥር ባለሙዎች እና የስራ ኃላፊዎች በምግብ በመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ሕገወጥን እንዴት መከላከልና መቆጣጠር እንደሚችሉ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ የጤና ቁጥጥር ዘርፉ ከፍትህ አካላት ጋር እንዴት በቅንጅት መስራት እንደሚቻል አቅጣጫ ለመቀየስ፣  ሕገወጥ ንግድ ሲከሰት መረጃዎች እንዴት ሊሰበሰቡ እንደሚገባና  መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ግንዛቤ ለመፍጠር አላማ አድርጎ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ታውቋል፡፡
ለሰልጣኞች የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተቋቋማባቸው ህጎች፣ በሸማቾች ጥበቃ አዋጅን፣ በኢንተለጀንስ እና ሰርቪላንስ አሰራርን በተመለከተ እና  በምግብ፣ በመድኃኒት እና በጤና አገልግሎት  የቁጥጥር ህጎች እንዲሁም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶችና ነባራዊ ሁኔታ ስልጠናዎች  ተሰጥተዋል፡፡
ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች እንደገለጹት በዘርፉ ባሉ ሕጎች ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዳገኙ እና በአሁኑ ጊዜ ሕገወጥ ቁጥጥርን ለመከላከል የሚያስችሉ የጋራ አሰራሮች እንዴት ሊከናወኑ እንደሚገባ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በመጨረሻም ሁለቱም ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተቀናጅቶ ለመስራት የስምነት ሰነድ ተፈርሟል፡፡

 

Comments / Feedback  •   • 

Note: To view, save/download, or print the following files, you must have Adobe Acrobat Reader installed on your computer.
Click here to download Adobe Acrobat Reader.