ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለፌዴራልና ክልል ተቆጣጣሪ አካላት ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመላ ሀገሪቱ ለተውጣጡ አንድ መቶ የምግብ ተቋማት ተቆጣሪዎች በምግብ ተቋማት የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ፣ የምግብ ተቋማት የኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር እና ሌሎች ዕርሰ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ በሄልዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል የሚሰጠው ስልጠና የተጀመረ ሲሆን ስልጠናውም ከህዳር 5 እስከ 9/2011 ዓ.ም. ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን…