በትንባሆ ቁጥጥር ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት የቀረበ ጥሪ፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ፣ መደኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 8 መሰረት ባለስልጣኑ የትምባሆ ቁጥጥርን በተመለከተ ረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ በመሆኑ በረቂቁ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥበት የመመሪያውን ቅጂ ከእዚህ በታች ያያዝን መሆኑን እየገለጽን አስተያየታችሁን እስከ ህዳር 3 ቀን 2013 ከቀኑ 9፡00 ድረስ በጽሑፍ ለባለስልጣኑ የህግ ክፍል ወይም በኢ-ሜል contactefda@efda.gov.et ወይም በፖስታ ቁ. 5681 እንድትልኩ በአክብሮት ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ ለበለጠ መረጃ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል መጠየቅ ሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡