1. “ምግብ”
ማለት
በአዋጁ
አንቀጽ
2
ንዑስ
አንቀጽ
1
መሰረት
የተሰጠው
ትርጓሜ
እንደተጠበቀ ሆኖ በምግብ አምራች ድርጅት ተመርቶ ከአንድ ክልል በላይ ወይም ለውጪ
አገር ገበያ ሽያጭ የተዘጋጀ ምርት ነው፤
2. “የጨቅላ ህፃናት ምግብ” ማለት ከእንስሳ ወይም ከእጽዋት የሚገኝ ወተት ወይም ወተት
መሰል ውጤት ሆኖ አግባብ ባለው የጨቅላ ህፃናት ምግብ ደረጃ መሰረት በፋብሪካ
የተዘጋጀና ከውልደት እስከ ስድስት ወር እድሜ ላሉ ጨቅላ ህፃናት የንጥረ ምግብ ፍላጎትን
ለሟሟላት የተዘጋጀ ምግብ ነው፤
3. “የታዳጊ ህፃናት ምግብ” ማለት ከእንስሳ ወይም እጽዋት የሚገኝ ወተት ወይም ወተት
መሰል ውጤት ሆኖ አግባብ ባለው የህፃናት ምግብ ደረጃ መሰረት በፋብሪካ የተዘጋጀ
ከስድስት ወር እስከ ሶስት አመት የሆነን ህፃንን ለመመገብ ተስማሚ እንደሆነ የተገለፀ
ወይም በሌላ መልኩ ገበያ ላይ የዋለ ምግብ ነው፤
4. “ተጨማሪ ምግብ” ማለት ማንኛውም መደበኛ አመጋገብን የንጥረ ምግብ ፍላጎት ለማሟላት
የሚዘጋጅ የንጥረ ምግብ ወይም ፊዚዮሎጂካል ውጤት ያላቸው የቫይታሚን ወይም
የማዕድን ወይም የሌሎች ንጥረ ነገሮች በነጠላ ወይም በጣምራ የሚገኙበትና በተወሰነ
መጠን እንዲወሰድ ታስቦ በካፕሱል፣ በእንክብል፣ በዱቄት፣ በፈሳሽ፣ በጠብታ ወይም በሌላ
ተመሳሳይ ሁኔታ የሚዘጋጅ የምግብ ዓይነት ነው፤
5. “የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት በምግብ ንግድ ሥራ ላይ የሚሰማራ ድርጅት
አስፈላጊውን ድርጅታዊ መስፈርት አሟልቶ ሲገኝ በባለሥልጣኑ አካል የሚሰጥ የሥራ
ፈቃድ ነዉ