በምግብ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩና የሚሰማሩ ድርጅቶች የሚልኩት፣ የሚያስመጡት
ወይም የሚያከፋፍሉትን ምግብ ጥራትና ደህንነቱን በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤና
መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦች ጥራታቸውንና ደህንነታቸው የተረጋገጠ እና አግባብ
ያለውን መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአሰራር ግልፅነትና ተጠያቂነት ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡
ማንኛውም በምግብ ንግድ ስራ ላይ ለሚሰማራ ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ
ምስክር ወረቀት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ
ቁጥር 661/2002 አንቀፅ 55 (3) እና የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ
አስተዳደርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀፅ 98 መሰረት ይህ የምግብ ላኪ፣
አስመጪና ጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ ወጥቷል፡: