የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡት አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የጤና ባለሙያዎችን ምዝገባና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና የቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ባለስልጣኑም ከተሰጡት ስልጣንና ኃላፊነቶች መካከል በበቂ መጠን በገበያ ላይ የማይገኙ የጤና ባለሙያዎችንና ከውጭ ሀገር የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚመጡ ባለሙያዎችን መመዝገብና የሙያ ስራ ፈቃድ መስጠትና መቆጣጠር አንዱ በመሆኑ፤ በመሆኑም በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 3 እና ደንብ ቁጥር 299/2006 መሰረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡት አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የጤና ባለሙያዎችን ምዝገባና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና የቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ባለስልጣኑም ከተሰጡት ስልጣንና ኃላፊነቶች መካከል በበቂ መጠን በገበያ ላይ የማይገኙ የጤና ባለሙያዎችንና ከውጭ ሀገር የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚመጡ ባለሙያዎችን መመዝገብና የሙያ ስራ ፈቃድ መስጠትና መቆጣጠር አንዱ በመሆኑ፤ በመሆኑም በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 3 እና ደንብ ቁጥር 299/2006 መሰረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡