የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ ክትባት ወይም መድኃኒት አለው?

እስካሁን ድረስ ለዚህ በሽታ መከላከያ ክትባትም ሆነ መፈወሻ መድኃኒት የለውም፡፡ ሆኖም ተመራማሪዎች ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባትና መፈወሻ መድኃኒት ለማግኝት ሌት ከቀን እየሠሩ ሲሆን ውጤት ተገኝቶ አገልግሎት ላይ ለማዋል ብዙ ወራቶችን ስለሚጠይቅ አሁንም መንግሥትና የጤና ባለሙያዎች የሚነግሩንን ምክር ተቀብለን ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው፡፡

የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታን መከላከል ይቻላል? እንዴት?

የሚከተሉትን በጥንቃቄ በመፈጸም አዎ ይቻላል፡፡ 1)  እጅን በውሀ እና በሳሙና  ቶሎ ቶሎ በአግባቡ መታጠብ፣ ውሀና ሳሙና በአካባቢያችን ከሌለ ደግሞ የእጅ ማጽጃ ኬሚካሎችን (Hand sanitizer) በመጠቀም እጅን በደንብ ማጽዳት፤ 2) አለመጨባበጥ 3) አካላዊ ርቀትን መጠበቅ (ቢያንስ 2 የአዋቂ እርምጃ ወይንም 2 ሜትር ርቀት ጠብቀው መንቀሳቀስ)

የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታን ይከላከላሉ?

በአሁኑ ወቅት ከኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ መከሰት ጋር ተያይዞ የተለያዩ ሀገራትና ብዙኃን መገናኛ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ተከትሎ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ዜጎች የተለያዩ  የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን ሲጠቀሙ ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ከበሽታው አደገኛነት ጋር ተያይዞ ስለምንጠቀምባቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ምንነት፣ ከምን እንደተሠሩ፣ የት እንደተሠሩ፣…

የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል ምን ዓይነት የእጅ ማጽጃ (Hand sanitizer) ልጠቀም?

ማንኛውም በሕጋዊ መንገድ የተመረተ ወይንም ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የእጅ ማጽጃ (Hand sanitizer) የአልኮል መጠኑ ቢያንስ 80 በመቶ (80%) እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተላላፊ የሆኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን የመከላከል አቅም ያለው ስለሆነ መጠቀም ይቻላል፡፡

ከጨርቅ የተሠራ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ከኮሮና ቫይረስ ራሴን ለመጠበቅ ይረዳኛል?

የኮሮና ቫይረስ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን በዓይን የማይታዩ በጣም ረቂቅ ስለሆኑ በቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚዘጋጁ የፊት ጭንብሎች በበሽታው ከተያዘ ሰው የሚወጡ በቫይረሱ የተበከሉ የእርጥበት ቅንጣቶችን መከላከል እንደማያስችሉ የተለያዩ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ  በኩል ደግሞ ሀገራት እነዚህን ከጨርቅ የተሠሩ የፊት ጭንብሎች በማህበረሰቡ ቢደረጉ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ስለሚረዳ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙበት ቦታዎች ጭምብል ቢጠቀሙ…

ሕጋዊ ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የፊት መሸፈኛ ጭምብል (Medical mask) እና N95 የመተንፈሻ የሕክምና ጭንብል (Surgical N95 respirator) አምራቾችና አስመጪዎችን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የፊት መሸፈኛ ጭምብል (Medical mask) እና N95 የመተንፈሻ የሕክምና ጭንብል (Surgical N95 respirator) አምራቾችና አስመጪዎችን እውቅና እንዲሰጥ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ሲሆን ብቃታቸውን አረጋግጦ እንዲያመርቱ ወይንም እንዲያስመጡ ፈቃድ የሰጣቸውን ተቋማትና የምርቱን ስም ይህንን https://eris.efda.gov.et/public/temporary_coc በመጫን ይመልከቱ፡